‹‹ሰሚው አላህ››‹‹ተመልካቹ አላህ››

‹‹ሰሚው አላህ››‹‹ተመልካቹ አላህ››
ድምጾችን ሁሉ ደካማውንና ጯኺውም የሚሰማ። አንዱ ድምጽ ከሌላው ድምጽ፣የአንዱ ጥያቄና ልመና የሌላውን ከመሰማት የማያውከው ሰሚው አላህﷻ  ነው። ‹‹ሰሚው ተመልካቹ›› . . የምትናገረውን ይሰማልና ራስህን መርምር ተቆጣጠር፤ጸሎትህን ያዳምጣልና ጌታህን ተማጸነው። ከርሱ የሚሰወር ምንም ነገር ስለሌለ ሥራህን ሁሉ ይመለከታልና በጎ በጎውን ሥራ፤እርሱ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና። ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ሌሊት ጥቁር ጉንዳን ቋጥኝ ድንጋይ ላይ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ይመለከታል፤ከሰባቱ ሰማያት በላይ ያለውን ሁሉ እንደሚያይ ከሰባት መሬቶች በታች ያለውንም ያያል። ‹‹ሰሚው ተመልካቹ›› ከርሱ የሚሰወር ምንም ነገር የለም፤ከእይታው የሚደበቅ መጪም ሆነ ሂያጅ የለም።

Tags: