በአላህ ማመን ሲታጣ . .

በአላህ ማመን ሲታጣ . .
በአላህ ማመን በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ከተደበላለቁ አምኮዎች፣እውነተኛ አምልኮ ወደሚገባው አላህ ﷻ አምልኮ የሚደረግ ሽግግር ነው።

በብዙ ሰዎች ሕይወት ውስጥ የኢማን መክፈቻ ቁልፍ ሲጠፋ አይቀሬ ውጤቱ ጭንቀትና መከራ ይሆናል። ይህም ከመከራና ስቃይ ሕይወት ለመገላገል ይችሉ ዘንድ፣አንዳንድ ሕብረተሰቦች ራስን ለመግደል የሚረዱ አዳዲስ ስልቶችንና ዘዴዎችን በተራቀቀ መንገድ ወደመፍጠር ደረጃ አድርሷቸዋል። በእስላም ታላቅ ጸጋ አላህ የተመሰገነ ይሁን - አልሐምዱ ሊልላህ። ጸጋም በዚህ በቃ። ይህን ዜና እንካችሁ፦

ከዓለም ለመሰናበት አዲስ መንገድ፦

በአውስትራሊያ የእዝነት ግድያ ሰባኪ የሆነው ፊሊፕ ኒችኬ እንደሚለው፣ ‹‹የመሰናበቻው ሻንጣ›› የሚል ስያሜ የተሰጠውና ከካናዳ በፖስታ አማካይነት ታዞ የሚመጣው የራስን ሕይወት የማጥፊያ መሣሪያ፣በአገሪቱ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ በመሸጥ ላይ ይገኛል።

የመሣሪያው ዋጋ 30 የአሜሪካ ዶላር ሲሆን፣ከፕላስቲክ የተሠራና በመታነቅ አማካይነት የሚገድል ልዩ ሻንጣ አብሮት ይመጣል።

ኒችኬ ለአውስትራሊያው የኤቢሲ ጣቢያ በሰጠው መግለጫ፣መሣሪያው በተወሰነ ደረጃ አስከፊ ይመስላል፣ይሁን እንጂ ነፍስ ለማውጣት ግን በጣም ውጤታማ ነው።

መሣሪያው በጣም ስፋት ባለው ሁኔታ አገልግሎት ላይ እየዋለ ሲሆን፣ስለ መሣሪያው ስለ አጠቃቀሙና ከዚህ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች በየቀኑ ብዙ ሰዎች እንደሚያነጋግሩት አክሎ ገልጿል።

በሌላ በኩል ደግሞ፣የነርቭ ሥርዓትን በመጉዳት የመንቀሳቀስ ችሎታን በሚያሳጣ በሽታ የተያዘች አንዲት እንግሊዛዊት፣ሕይወቷን በገዛ እጇ ስታጠፋ ባለቤቷ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግላት ለማስገደድ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ክስ መስርታለች።

ቢቢሲ እንዳስታወቀው ዕድሜዋ 42 የሆነው ዳያና ቢሪቲ፣በዚህ በሽታ የተያዘችው ከሁለት ዓመት በፊት ሲሆን፣ወደ ፍርድ ቤት መሄድ የተገደደችው ባለቤቷ ራሷን ስትገድል እገዛ ካደረገላት ባለ ሥልጣናት ከሕግ ተጠያቂነት ነጻ እንደሚሆን ዋስትና አንሰጥም ካሏት በኋላ ነበር።

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

{وَمَنۡ أَعۡرَضَ عَن ذِكۡرِي فَإِنَّ لَهُۥ مَعِيشَةٗ ضَنكٗا وَنَحۡشُرُهُۥ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ أَعۡمَىٰ ١٢٤}

‹‹ከግሣጼም የዞረ ሰው፣ለርሱ ጠባብ ኑሮ አልለው፤በትንሣኤም ቀን ዕውር ኾኖ እንቀሰቅሰዋለን።››

]ጣሃ፡124[Tags: