ተብቃቂው አብቃቂው ባለጸጋው አላህ . .

ተብቃቂው አብቃቂው ባለጸጋው አላህ . .
በርሱነቱ ከማንም እና ከምንም በራሱ የተብቃቃ። የፍጹማዊ ተብቃቂነትና የምሉእ ጸጋ በባለቤት የሆነ። ባሕርያቱና ምሉእነቱ በምንም መልኩ ፈጽሞ ለጉድለት የማይጋለጥ። ተብቃቂቱና ፍጸጹማዊ ባለጸጋነቱ ከርሱነቱና ከሕልውናው መገለጫዎች አንዱ በመሆኑ ከማንምና ከምንም የተብቃቃ መሆኑ የግድ የሆነ። ፈጣሪ፣ሁሉን ቻይ፣ሲሳይን ሰጭና መጽዋች መሆኑም እንዲሁ የግድ ነው። በምንም መልኩ ከማንም ምንም አይፈልግም። የሰማያትና የምድር፣የዱንያና የኣኽራ ሀብት መጋዝኖች ሁሉ በእጁ የሆነ በራሱ የተብቃቃ ጌታ ነው።Tags: