አላህ ﷻ ፦

አላህ ﷻ  ፦
አላህ ﷻ . . በብዛት የሚወደስና የሚመለክ አምላክ . .

ሰማያትና በውስጣቸው ያለው ሁሉ፤መሬቶችና ያሉባቸው ሁሉ እርሱን በማጥራት ያወድሱታል . .

ሌሊትና ከዋክብቱ፣ቀንና ብርሃኑ . . የብስና ባሕሩ . . ያጠሩታል፤ያወድሱታል፤ይቀድሱታልም።

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(وَإِن مِّن شَيۡءٍ إِلَّا يُسَبِّحُ بِحَمۡدِهِۦ وَلَٰكِن لَّا تَفۡقَهُونَ تَسۡبِيحَهُمۡ)

‹‹ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያጠራው (የሚያወድሰው) እንጂ አንድም የለም፤ግን ማጥራታቸውን አታውቁትም፤እርሱ ታጋሽ መሓሪ ነው፡፡››

]አልእስራእ፡44[

‹‹አላህ››ﷻ ከሚታወቁት ሁሉ ይበልጥ ታዋቂ ነውና ማስተዋወቅ አያሻውም . . ልቦች ያውቁታል፣ነፍሶችም እርሱን ለማወቅ ይፍረከረካሉ።

‹‹አላህ››ﷻ ልቦች ያመልኩታል፤ነፍሶች ምሕረቱን ይጠባበቃሉ፤ፍጥረታት በርሱ ውዳሴ ይጽናናሉ፣ይረጋጋሉ።

አላህ ﷻ ሃማኖታዊ ግዴታ በሚጸናባቸው አገልጋዮቹ ልብ ውስጥ፣ወደርሱ በመጠጋት ብቻ እንጂ የማይሰበሰብ መበታተንና መባዘንን፣ እርሱ ብቻ እንጂ ሌላ ሊያብቃቃው የማይቻል ድህነትን አድርጓል።

‹አላህ››ﷻ የሚለው ቃል በሁሉም መልካም ባሕርያት የሚገለጸው መለኮታዊ እርሱነት (ዛት) የሚጠራበት ስሙ ነው።

ለባሮቹ አላህ ﷻ አስፈላጊያቸው መሆኑ ፦

ባሪያው በችግርና መከራ ጊዜ የሚጠጋበትንና ከለላ የሚሰጠውን የሚፈልግ ሲሆን ይህ ተፈጥሯዊ ባሕርይው ነው። ለዚህ ነው ነገ የሚገናኘውና ከፊቱ የሚቆም በመሆኑ በሁሉም ሁኔታዎቹ ውዴታውን ለማግኘት የሚጥረውና ፈጣሪ ጌታው ሁሌም አስፈላጊው መሆኑን ከውስጡ የሚገነዘበው።

አገልጋዩ ለአላህ ﷻ ተናንሶ ግዴታዎቹን ሁሉ ከተወጣ፣የአላህ ቀጠሮ እውነት መሆኑን አረጋግጦ ከታገሰ፣ሰዎችን በጌታው ትእዛዝ ከሚመሩ መሪዎች አንዱና ሌሎች የሚከተሉት አርአያ እንዲሆን ያደርገዋል።

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(وَجَعَلۡنَا مِنۡهُمۡ أَئِمَّةٗ يَهۡدُونَ بِأَمۡرِنَا لَمَّا صَبَرُواْۖ وَكَانُواْ بِئايَٰتِنَا يُوقِنُونَ ٢٤)

‹‹በታገሡና በታምራቶቻችን የሚያረጋግጡ በኾኑም ጊዜ፣ከነርሱ በትእዛዛችን የሚመሩ መሪዎችን አደረግን።››

[አልሰጅዳህ፡24]

ለዚህም ነው አላህ ﷻ ትዕግሥትንና እርግጠኝነትን (የቂንን)፣በሃይማኖቱ ውስጥ ግንባር ቀደም የመሪነት ቦታ ለመያዝ ምክንያት ያደረገው።

እርሱን ማወቅ ቀላል አድርጎ የገራለት መሆኑ፣አላህ ﷻ ለባሪያው የዘረጋለት ጸጋና ቸርነት ነው።

የፍጡራን በፈጣሪ አምላክ ላይ መንጠላጠልና እርሱን መማጸን አብሯቸው የተፈጠረ ሲሆን፣ደግ የዋለላቸውን፣ችሮታውን የዘረጋላቸውን አላህን ﷻ መውደድና ማፍቀር እንዲሁ ተፈጥሯዊ ባሕርያቸው ነው።

ከኢማን ውጭ ያለው ስንቅ ሁሉ አላቂ ነው፤ከአላህ በስተቀር ከሌላ የሚመጣ ድጋፍና እገዛ ሁሉ ወዳቂ ነው።

የዕውቀት ክቡርነት፦

የዕውቀትና የትምህርት ክቡርነት ከሚቀሰመው ዕውቀትና ከመረጃው ክቡርነት የሚመነጭ ነው። ከፈጣሪ ጌታ ﷻ የበለጠ ክቡር የሆነ፣ባሕርያቱን፣መልካም ስሞቹን፣ጥበቡንና በፍጡራኑ ላይለውን መብቱን ከማወቅ የበለጠ ክቡር ዕውቀትም የለም። ለዚህ ነው ተውሒድ የሃይማኖት አስኳል የሆነው። ከቅዱስ ቁርኣን አንድ ሦስተኛ የሚሆነው የአላህን አንድነትና ተውሒድን በግልጽ የሚያረጋግጥ ነው።

በሁሉም ነገር ውስጥ አንድነቱን የሚያመለክት ታምር አለ ፦

አላህ ﷻ በፍጥረታቱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ለሕልውናው፣ለተውሒዱ፣ለምሉእነቱ፣ ለግርማ ሞገሱና ለኃያልነቱ ማስረጃ አድርጓል። በተጨማሪም እነዚህን ማስረጃዎች እንድናስተውልና እንድናስተነትን ያዘዘ ሲሆን፣አርቀው ለሚያስተውሉና ለሚመራመሩ የአእምሮ ባለቤቶች ምልክቶች መሆናቸውንም ነግሮናል።

አስተዋዮችንና የአእምሮ ባለቤቶችን፣በራሱ የተብቃቃ በሆነው አንድ አምላክ አላህ ﷻ እንዲያምኑ ጥሪ የሚያደርጉ አንዳንድ አንቀጾችን ለመውሰድ የአላህን መጽሐፍ ቁርኣንን በጨረፍታ እንጎበኛለን። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(وَفِي ٱلۡأَرۡضِ ءَايَٰتٞ لِّلۡمُوقِنِينَ ٢٠ وَفِيٓ أَنفُسِكُمۡۚ أَفَلَا تُبۡصِرُونَ ٢١)

‹‹በምድርም ውስጥ፣ለሚያረጋግጡ ሰዎች ምልክቶች አልሉ፡፡ በነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ታዲያ አትመለከቱምን?››

[አልዛሪያት፡20-21]

በተጨማሪም ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(قُلِ ٱنظُرُواْ مَاذَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ)

‹‹፦ በሰማያትና በምድር ያለውን (ታምር) ተመልከቱ፣በላቸው፤››

[ዩኑስ፡101]

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۖ مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ إِذۡنِهِۦۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُوهُۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ٣ إِلَيۡهِ مَرۡجِعُكُمۡ جَمِيعٗاۖ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقًّاۚ إِنَّهُۥ يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ بِٱلۡقِسۡطِۚ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَهُمۡ شَرَابٞ مِّنۡ حَمِيمٖ وَعَذَابٌ أَلِيمُۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡفُرُونَ ٤ هُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ ٱلشَّمۡسَ ضِيَآءٗ وَٱلۡقَمَرَ نُورٗا وَقَدَّرَهُۥ مَنَازِلَ لِتَعۡلَمُواْ عَدَدَ ٱلسِّنِينَ وَٱلۡحِسَابَۚ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۚ يُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ ٥ إِنَّ فِي ٱخۡتِلَٰفِ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَمَا خَلَقَ ٱللَّهُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَّقُونَ ٦)

‹‹ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፤ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲኾን፣በዐርሹ ላይ ተደላደለ፤ከርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፤ይሃችሁ አላህ ጌታችሁ ነውና ተገዙት፤አትገሠጹምን? ሁላችሁም ኾናችሁ መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው፤(ይህም) የተረጋገጠ የአላህ ቃል ኪዳን ነው፤እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ከዚያም እነዚያን ያመኑትንና መልካም የሠሩትን በትክክል ይመነዳ ዘንድ ይመልሰዋል፤እነዚያ የካዱትም፣ይክዱት በነበሩት ነገር ለነርሱ ከፈላ ውሃ የኾነ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አላቸው። እርሱ ያ ፀሐይን አንጸባራቂ፣ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፤የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፤አላህ ይህንን በእውነት እንጂ (በከንቱ) አልፈጠረውም፤ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡ ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው፣አላህም በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ፣ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ምልክቶች አልሉ፡፡››

[ዩኑስ፡3-6]

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(إِنَّ فِي خَلۡقِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَٱخۡتِلَٰفِ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ لَأٓيَٰتٖ لِّأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ ١٩٠ ٱلَّذِينَ يَذۡكُرُونَ ٱللَّهَ قِيَٰمٗا وَقُعُودٗا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمۡ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلۡقِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ رَبَّنَا مَا خَلَقۡتَ هَٰذَا بَٰطِلٗا سُبۡحَٰنَكَ فَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ ١٩١)

‹‹ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር፣ሌሊትና ቀንም በመተካካት፣ለባለ አእምሮዎች ምልክቶች አሉ። (እነርሱም) እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣በጎኖቻቸው ተጋድመውም፣አላህን የሚያወሱ፣በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ ፦ ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ጥራት ይገባህ፤ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን የሚሉ ናቸው።››

[ኣል ዒምራን:190-191]

በተጨማሪም አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(وَفِي خَلۡقِكُمۡ وَمَا يَبُثُّ مِن دَآبَّةٍ ءَايَٰتٞ لِّقَوۡمٖ يُوقِنُونَ ٤)

‹‹እናንተንም በመፍጠር፣ከተንቀሳቃሽም (በምድር ላይ) የሚበትነውን ሁሉ (በመፍጠሩ)፣ለሚያረጋግጡ ሕዝቦች ታምራቶች አልሉ።››

[አል ጃሢያ፡4]

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(أَفَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَتَكُونَ لَهُمۡ قُلُوبٞ يَعۡقِلُونَ بِهَآ أَوۡ ءَاذَانٞ يَسۡمَعُونَ بِهَا)

‹‹ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች፣ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች፣ይኖሩዋቸው ዘንድ፣በምድር ላይ አይሄዱምን?››

[አል ሐጅ፡46]

በተጨማሪም አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(أَفَلَمۡ يَنظُرُوٓاْ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَوۡقَهُمۡ كَيۡفَ بَنَيۡنَٰهَا وَزَيَّنَّٰهَا وَمَا لَهَا مِن فُرُوجٖ ٦)

‹‹ወደ ሰማይም፣ከበላያቸው ስትኾን ለርሷ ምንም ቀዳዳዎች የሌሏት ኾና እንዴት እንደ ገነባናትና (በከዋክብት) እንዳጌጥናት አልተመለከቱምን?››

[ቃፍ፡6]

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(صُنۡعَ ٱللَّهِ ٱلَّذِيٓ أَتۡقَنَ كُلَّ شَيۡءٍ)

‹‹የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ (ተመልከት)፤››

[አል ነምል፡88]

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّأُوْلِي ٱلنُّهَىٰ ٥٤)

‹‹በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ ታምራት አለበት።››

[ጣሃ፡54]Tags: