ከአላህ ከስሞቹና ከባሕርያቱ ጋር መኖር

ከአላህ ከስሞቹና ከባሕርያቱ ጋር መኖር
በራሱ ላይ እዝነትን ጽፏል። እዝነቱ ከቁጣው ቀድሟል። እዝነቱና ችሮታው ለነገሮች ሁሉ የተዘረጋና ተደራሽ ነው . . (إِنَّ رَحۡمَتَ ٱللَّهِ قَرِيبٞ مِّنَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ٥٦)

‹‹የአላህ ችሮታ ከበጎ አድራጊዎች ቅርብ ነውና።›› [አልአዕራፍ፡56]


ቁሳዊ ሲሳይና ሕሊናዊ ሲሳይ ይለግሳል፤በችሮታውና በደግነቱ ይሰጣል። ከልገሳዎቹ መካከል አላህ ለባሪያው አእምሮው ውስጥ የሚከፍትለት መልካም ሃሳቦች፣ጠቃሚ ግንዛቤዎች፣ዕውቀት፣ቅን መመሪያ፣ስኬታማነትና የዱዓው ተቀባይ መሆን . . ይገኙበታል። እነዚህና ሌሎቹም አላህﷻ ለብዙ ሰዎች የቸራቸው ሕሊናዊ ሲሳይ ናቸው።
በባሕርያቱ ምሉእ . . በስሞቹ ታላቅ፣ምስጋና እና ውዳሴው ገደብ የሌለው፣ኃያልነቱ፣ግዛቱ፣ሥልጣኑ፣ትሩፋቱ፣ቸርነቱና ደግነቱ የሰፋና እጅግ የገዘፈ ችሮታ ሰፊ። ‹‹ችሮታ ሰፊው›› . . በስጦታው፣በበቂነቱ፣በዕውቀቱ፣በከባቢነቱ፣በጥበቃውና በቅንብሩ ለፍጥረታቱ ሁሉ የሰፋ ነው።
‹‹በጣም ወዳዱ›› . . ነቢዮቹን፣መልእክተኞቹንና ተከታዮቻቸውንም የሚወድና የሚወዱት፤ከምንም በላይ እነርሱ ዘንድ ተወዳጅ የሆነ፣ልቦቻቸው በርሱ ፍቅር የተሞላ፣ምላሶቻቸው በርሱ ውዳሴ የሚርገበገቡ፣ውስጣቸው በሁሉም ገጽታ በርሱ ፍቅር ለርሱ ፍጹም በመሆንና ወደርሱ በመማለስ የተጠመደ።
ስብራትን ጠጋኝ፣እሰረኛን አጋዥ፣ድሃን ሀብታም የሚያደርግ፣የተሳሳቾችን ስህተቶች የሚያርምና የሚጠግን፣የኃጢአንን ኃጢአቶች የሚምር፣የሚሰቃዩትን ከስቃይ የሚገላግል፣የደጋግ ትጉሃን አፍቃሪዎቹን ልብ የሚጠግን።
የፍጥረተ ዓለም ውበት የርሱን ውበትና ግርማ ሞገሱን ያመለክታል። የርሱ ውበት አእምሮ የማያዳርሰው፣አኳኋኑ ከግንዛቤ በላይ የሆነ ነው። ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦
ዕውቀቱ ግልጹንና ስውሩን፣በምስጢር የሚነገረውንና በይፋ የሚነገረውንም፣ግዴታዎችን፣ሊሆኑ የማይችሉትንና ሊሆኑ የሚችሉትንም ሁሉ፣የላይኛውን ዓለምና የታችኛውንም ዓለም፣ያለፈውን የአሁኑን እና መጪውንም ሁሉ ያካበበ፣ምንም ነገር ከርሱ የማይሰወር።
ነፍስ በርሱ ቅርበት የምትጽናና፣በርሱ ውዳሴም የምትርገፈገፍ። ‹‹እርሱ ቅርቡ አላህ ነው . . ‹‹በጣም ቅርቡ›› . . በዕውቀቱ፣በውስጠ ዐዋቂነቱ፣በተቆጣጣሪነቱ፣በእይታውና ሁሉን ከባቢ በሆነው መረጃው ለእያንዳንዱ ፍጡር በጣም የቀረበ።
እስረኛው እስር ቤት ሆኖ፣የሰጠመው ባህር ውስጥ ሆኖ፣ደሃው ድህነቱ ውስጥ ሆኖ፣ወላጅ አልባው ህጻን በወላጅ አልባነቱ፣በሽተኛው በሕመሙ ውስጥ ሆኖ፣ልጅ ያጣው መካን በመካንነቱ እርሱን ይማጸናል። እርሱም ይሰጣል፣ይሰማል፣ይቀበላል፣ይፈውሳልም።
እርሱን ያወቁ ባሮቹን ልብ በኢማን ብርሃን፣ውስጣቸውን በቅን መመሪያ ያበራ።
በውሳኔውና በብያኔው ጥበበኛ፣ድሃውን ድሃ በማድረግ ወይም አንድን ሰው በሽተኛና ደካማ በማድረግ ውሳኔው ጥበበኛ የሆነ፣ቅንብሩ እንከን የሌለበት፣ቃሎቹም ሆኑ ተግባራቱ ጉድለትም ሆነ ዝንፈት የሌለበት፣እርሱﷻ የረቀቀና የላቀ ጥበብ ባለቤት ነው።
ማንኛውም ንጉሥና መሪ የርሱ ባሮችና አገልጋዮች የሆኑ የፍጹማዊ ንግሥና ባለቤት፣በሰማያትም ሆነ በምድር ያለው ትሩፋት ሁሉ የርሱ በረከትና የርሱ ጸጋ ብቻ የሆነ። (لَّهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ)

‹‹በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፤›› [አልበቀራህ፡225]


ልቦች ያጠሩት፣ተስፋዎች ሁሉ በርሱ ላይ የተንጠለጠሉ፣አንደበቶች በምስጋና ያጠሩትና ዘውትር የሚያወድሱት። ‹‹እርሱ ከጉድለት ሁሉ የጠራው ነው›› የበረከትና የጸጋዎች፣የትሩፋትና የውዳሴ ባለቤት የሆነ፣በረከቶች ከርሱ ወደርሱ የሆኑ፣ባሮቹን የሚባርክ በረከት፣የሻውን ጸጋና በረከት በማፍሰስ የሚባርካቸው።
ባሕርያቱ ከፍጥረታቱ ባሕርያት ጋር ከመመሳሰል ነጻ የሆኑ፣ከጉድለትና ከእንከን ሁሉ የራቁ፣ዕውቀቱ ምሉእና ነጻ የሆነ፣ፍትሑ አጠቃላይና ተደራሽ የሆነ፣ግዛቱ ከጉድለትና ከእንከን የነጻ ምሉእ የሆነ፣ፍርዱ ፍትሐዊና ነጻ የሆነ፣ሥራው የነጻና ሰላም የሆነ፣እርሱም ሰላም የሰላም ምንጭም እርሱ የሆነ፤የግርማ ሞገስና የክብር ባለቤት የሆነ ጌታ ላቀ።
በእርሱነቱና በባሕርያቱ እውነት፣ባሕርያቱ የተሟሉ፣መኖሩና ሕልውናው ከራሱ እርሱነት የመነጨ፣በርሱ ቢሆን እንጂ ማንኛውም ነገር ሕልውና የሌለው፣በግርማ ሞገስ በውበትና በፍጹማዊ ምሉእነት ሲገለጽ የኖረ ያለና የሚኖር፣በደግነትና በችሮታው ሲታወቅና እንደታወቀ የኖረና የሚኖር።
በእርሱነቱና በባሕርያቱ እውነት፣ባሕርያቱ የተሟሉ፣መኖሩና ሕልውናው ከራሱ እርሱነት የመነጨ፣በርሱ ቢሆን እንጂ ማንኛውም ነገር ሕልውና የሌለው፣በግርማ ሞገስ በውበትና በፍጹማዊ ምሉእነት ሲገለጽ የኖረ ያለና የሚኖር፣በደግነትና በችሮታው ሲታወቅና እንደታወቀ የኖረና የሚኖር።

‹‹ጸጥታን ሰጪው››እርሱ ጸጥታን ሰጪው፣ባሮቹን ጠባቂው አላህ ነው።

‹‹ጸጥታን ሰጪው››እርሱ ጸጥታን ሰጪው፣ባሮቹን ጠባቂው አላህ ነው።
 
2553
በባሮቹ መካከል ጸጥታን፣በፍጥረታቱ ዘንድ ደህንነትን፣በመለኮታዊ ራእዩ እርካታን የሚያሰራጭ።

‹‹ከፍርሃትም ያረካቸውን [ጸጥታ የሰጣቸውን]፣›› ባሮቹን በበላይነት የተቆጣጠረ፣አንበርክኳቸው በሥልጣኑ ስር ያደረገ፣የተንከባከባቸውና ድርጊቶቻቸውንና ሁኔታዎቻቸውን ያወቀ፣በዕውቀቱ ያካበባቸው፣ማንኛውም ነገር ለርሱ ገርና ቀላል የሆነ፣ለማንኛውም ነገር አስፈላጊው የሆነ።Tags:

 

ሁሌም በመሐሪነቱ የሚታወቀው፤ለባሮቹ ይቅርባይና ምሕረት ሰጭ በመሆን የሚገለጸው፤እያንዳንዱ ሰው የርሱን ይቅርታና ምሕረት፣እንደዚሁም እዝነቱንና ችሮታውን ለመፈለግ የሚገደደው ምሕረተ ብዙው አላህ።
ችሮታውና በደግነቱ ለባሮቹ ተጸጽቶ መመለስን (ተውበትን) የደነገገ፣ከዚህም አልፎ ክፉ ሥራን ወደ በጎ ሥራነት ለመቀየር ቃል የገባላቸው። ‹‹ጸጸትን ተቀባይ›› . . ባሮቹን በተውበታቸው ላይ እንዲጸኑ የሚያደርግ፣ግዴታቸውን ይወጡ ዘንድም የሚያግዛቸው።
አምልኮት በሚገባው አምላክነቱ አንድ ብቻ የሆነ፤ከርሱ በቀር በእውነት የሚመለከ ሌላ አምላክ የሌለ፤ይብዛም ይነስ ከዕባዳ ለርሱ ብቻ እንጂ ምንም ነገር ለማንምና ለምንም የማይዞር።
ፍጥረታት ሁሉ ከርሱ የሚፈልጉ እርሱ ግን ከማንም ምንም የማይፈልግ፣በራሱ ብቻ የተብቃቃ። (يُطۡعِمُ وَلَا يُطۡعَمُ)

‹‹የሚመግብ፣የማይመገብም ሲኾን፣›› [አልአንዓም፡14] ‹‹የሁሉ መጠጊያ›› . . አቀናባሪ ጌታ፣ያሻውን የሚፈጽም ፍጹማዊ ባለቤት። ‹‹የሁሉ መጠጊያ›› . . ልቦች ሁሉ ለጉዳዮቻቸውና ለችግሮቻቸው እርሱን ሲማጸኑ የሚሰጣቸውና የማይከለክላቸው። ሲለምኑት የሚሰማቸውና ችግራቸውን የሚያስወግድላቸው። ከርሱ የራቁት ሲጠሩት ሰምቷቸው ግንኙነቱን መላልሶ የሚቀጥልላቸው። የፈሩትንና የተሸበሩትን የሚያረጋጋና የሚያጽናና። በርሱ ላይ ተስፋ የጣሉትን ከግባቸው የሚያደርስ። አደጋ የተጋረጠባቸውን ነጻ የሚያወጣ። ባሮቹን በአምልኮው ሲተጉ ከፍ የሚያደርጋቸው።


‹‹አሸናፊው››

‹‹አሸናፊው››
 
3141
ፍጹማዊ አሸናፊት የርሱ ብቻ የሆነ፤ፍጥረታት ሁሉ ለርሱ የሚዋደቁለትና የሚንበረከኩለት፣ኃይለኛ ሁሉ እርሱ ፊት ተዋራጅ የሆነ። ‹‹አሸናፊው›› አሸናፊነትን እርሱ ለሚሻው ሰው የሚሰጥ፣ከሻው ሰውም የሚነጥቅ፣ያሻውን ሰው የሚያዋርድና በጎው ሁሉ በርሱ እጅ የሆነ። አላህﷻ እንዲህ ብሏል፦

Tags:

 

‹‹የበላይ አሸናፊ››

‹‹የበላይ አሸናፊ››
 
2892
እምቢተኞችንና ትእቢተኞችን በታላላቅ ማስረጃዎች ዝም አስኝቶ፣አምላክነት ጌትነት መልካም ስሞችና የመጠቁ ባሕርያት ተገቢው መሆናቸውን ያረጋገጠላቸው የበላይ አሸናፊ። ‹‹የበላይ አሸናፊ›› ግፈኞችን፣አምባገነኖችንና እብሪተኞችን አንበርክኮና አንኮታክቶ የሚያዋርድ።

Tags:

 

የፍጥረታቱ ሲሳይና ምግባቸው በርሱ እጅ የሆነ። ለሻ ሰው ሲሳይ የሚያፋሰና ባሻው ሰው ላይ የሚያጠብ። ነገሮችን ሁሉ የሚያቀነባብር፣የሰማያትና የምድር ድልብ ሀብት መክፈቻ በእጁ የሆነ ሲሳይ ሰጪ ጌታ። አላህﷻ እንዲህ ብሏል፦
የሁሉንም ነገሮች ድብቅ ምስጢር የሚያውቅ፣ረቂቅ ሥራዎችን ሁሉ የሚቆጣጠር፣ቀንም ሆነ ማታ ምንም ነገር ከርሱ የማይሰወር፣የባሮቹን ጥቅሞች ጥቃቅኑንና ውስብስቡን ሁሉ የሚያውቅና የሚያዝንላቸው። ‹‹እዝነተ ረቂቁ›› ነገሮችን ሲወስን ለባሮቹ የሚራራ፣ወሳኔውን ሲያስተላልፍ ረድኤቱን የሚቸራቸው። ችግር ሲጠና እና መከራ ሲበረታ የመፍትሔ በሮችን የሚከፍትላቸው፣ነገሮች ሲወሳሰቡ የሚያገራላቸው።
እዝነትና የቸርነት በሮቹን በሰፊው የሚከፍት። በባሮቹ ላይ ጸጋና በረከቱን ደግሞ ደጋግሞ የሚያዘንብ። የዕውቀትና የጥበብ ብርሃንን አእምሯቸው ውስጥ የሚያፈነጥቅ። ልቦች በርሱ ያምኑ ዘንድ የቅን መመሪያ በሮቹን የሚከፍትላቸው።
በርሱነቱ ከማንም እና ከምንም በራሱ የተብቃቃ። የፍጹማዊ ተብቃቂነትና የምሉእ ጸጋ በባለቤት የሆነ። ባሕርያቱና ምሉእነቱ በምንም መልኩ ፈጽሞ ለጉድለት የማይጋለጥ። ተብቃቂቱና ፍጸጹማዊ ባለጸጋነቱ ከርሱነቱና ከሕልውናው መገለጫዎች አንዱ በመሆኑ ከማንምና ከምንም የተብቃቃ መሆኑ የግድ የሆነ። ፈጣሪ፣ሁሉን ቻይ፣ሲሳይን ሰጭና መጽዋች መሆኑም እንዲሁ የግድ ነው። በምንም መልኩ ከማንም ምንም አይፈልግም። የሰማያትና የምድር፣የዱንያና የኣኽራ ሀብት መጋዝኖች ሁሉ በእጁ የሆነ በራሱ የተብቃቃ ጌታ ነው።

 


ፍጥረታቱ ሁሉ ቀለባቸውን የሚያደርስላቸው። የሚያኖራቸውንና የሚኖሩበትን ያመቻቸላቸው። ርሃብና ጥማታቸውን የሚያስወግድላቸው። የተድላ ሕይወት እንዲኖሩ የሚያደርጋቸው። ሁሉን ቻይ አኑዋሪና ቀላቢ አምላክ።

 


ልክተኛውን ﷺ በመላክና በገላጩ መጽሐፍ

ለባሮቹ እውነተኛውን ቀጥተኛ መንገድ ያሳየ ጌታ።


በባሮቹ ላይ ተጠባባቂና ሥራዎቻቸውን መርማሪው አላህﷻ ፣ ለበጎ ሠሪው መልካም ምንዳ ለክፉ ሠሪውም ተገቢ ቅጣቱን በዕውቀቱ መሰረት ዋጋቸውን የሚከፍል። (وَهُوَ أَسۡرَعُ ٱلۡحَٰسِبِينَ٦٢)

‹‹እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው።›› ለሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ለባሮቹ በቂያቸው የሆነ። በተለይ ደግሞ በርሱ ለአመነና በርሱ ላይ ለተማመነ፣ሃይማኖታዊም ሆኑ ዓለማዊ ጉዳዮቹን


ሎታው ምሉእ የሆነ፣በኃያል ችሎታው ፍጥረታትን ከምንም ያስገኘ። በችሎታው ነገሮቻቸውን ሁሉ ያቀነባበረ፣ያስተካከለና ያጸና። በችሎታው የሚያኖርና የሚገድል። ከሞት አስነስቶ ለሁሉም የሥራውን ዋጋ የሚሰጥ። በጎ ሠሪውን የሚሸልም፣ክፉ ሠሪውን የሚቀጣ። አንድን ነገር ሲሻ ኹን ሲለው የሚሆን። በኃያል ችሎታው ልቦችን እንዳሻውና ወደ ፈለገው መንገድ የሚገለባብጥ ጌታ።
ምድርንና በርሷ ላይ ያለውን ሁሉ የሚወርስ፣ከርሱﷻ በስተቀር ማንምና ምንም ቀሪ የማይኖር።
ድምጾችን ሁሉ ደካማውንና ጯኺውም የሚሰማ። አንዱ ድምጽ ከሌላው ድምጽ፣የአንዱ ጥያቄና ልመና የሌላውን ከመሰማት የማያውከው ሰሚው አላህﷻ  ነው። ‹‹ሰሚው ተመልካቹ›› . . የምትናገረውን ይሰማልና ራስህን መርምር ተቆጣጠር፤ጸሎትህን ያዳምጣልና ጌታህን ተማጸነው። ከርሱ የሚሰወር ምንም ነገር ስለሌለ ሥራህን ሁሉ ይመለከታልና በጎ በጎውን ሥራ፤እርሱ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና። ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ሌሊት ጥቁር ጉንዳን ቋጥኝ ድንጋይ ላይ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ይመለከታል፤ከሰባቱ ሰማያት በላይ ያለውን ሁሉ እንደሚያይ ከሰባት መሬቶች በታች ያለውንም ያያል። ‹‹ሰሚው ተመልካቹ›› ከርሱ የሚሰወር ምንም ነገር የለም፤ከእይታው የሚደበቅ መጪም ሆነ ሂያጅ የለም።
ርሱﷻ ጥቂቱን መልካም ሥራ የሚያመሰግን፣ብዙውን ጥፋት የሚምር፣ሥራዎቻቸውን ለርሱ ፍጹም ላደረጉ ትጉሃን ባሮቹን ያለ ገደብ ምንዳ የሚሰጥ አመስጋኙ አላህ ነው።

ተመስጋኙ አላህ

ተመስጋኙ አላህ
 
1909
በርሱነቱ ተመስጋኝ፣በሥራዎቹም ተመስጋኝ፣በምግባሩም ተመስጋኝ፣በቃሎቹም ተመስጋኝ የሆነ አምላክ። በዩኒቨርሱ ውስጥ ከአላህﷻ በስተቀር ሌላ ተመስጋኝ የለም፤ምሉእ ምስጋና ምሉእ ውዳሴ ለርሱ ብቻ ነውና።

Tags:

 

እርሱ በዝና፣በአሸናፊነት፣በኩራት፣በኃያልነትና በታላቅነት ባሕርያት የሚገለጽ፣የፍጥረታት ሁሉ የበላይ፣ትልቁ፣ታላቁ፣ባለ ግርማ ሞገሱ አላህ ነው። የወዳጆቹንና የምርጥ አገልጋዮቹን ልብ ለግርማ ሞገሱ፣ለታላቅነቱ፣ለኃያልነቱ፣ለርሱ ባላቸው ተገዥነትና ተዋራጅነት የሞላ አላህﷻ ነው።
በዐርሹ ላይ ተደላድሏል፤በሁሉም የኃያልነት፣ የታላቅነት፣የግርማ ሞገስና የውበት ባሕርያት የሚገለጽ ፍጹማዊ ምሉእ አምላክ ሆኗል።
ሕዝቦች ከከፊላቸው ሲሳይን ያዝ በማድረግ የሚፈትናቸው፣ሌሎቹን ይንበረከኩ ዘንድ ሲሳይን የሚከለክላቸው፣ሌሎቹን ደግሞ ደረጃቸውን ከፍ ለማድረግ ሲሳይ የሚያቆይባቸው ጌታ። ጥበቡ፣ቸርነቱ፣ደግነቱና ለጋሽነቱ በሚጠይቀው መሰረት ሲሳይን ለቀቅ አድርጎ የሚሰጥ፣ልቦችን በዕውቀት የሚቀልብ፣እጆቹን ዘርግቶ የሚለግስ ጌታ።
ርሱ የሰጠውን የሚከለክል፣እርሱ የከለከለውን የሚሰጥ የለም። ጥቅሞች ሁሉ የሚጠየቁትና የሚከጀሉት ከርሱ ነው። ለሚሻው ሰው የሚሰጠው እርሱ ነው፤በጥበቡና በእዝነቱ የሻውን ሰው የሚከለክልም እርሱ ነው።