በቤቱና በቤተሰቡ ፦

በቤቱና በቤተሰቡ ፦
1 - ለወላጆቹ የሚኖረው መልካም አያያዝ ፦

የተውሒድ ሰው ከማንም በላይ ለወላጆቹ ያለበትን ግዴታ በትጋት ይወጣል። አላህﷻ መጽሐፉ ውስጥ ተውሒድንና ለወላጆች ደግ መሆንን አንድ ላይ ሲያቆራኝ እንዲህ ብሏል ፦

(وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّآ إِيَّاهُ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنًاۚ إِمَّا يَبۡلُغَنَّ عِندَكَ ٱلۡكِبَرَ أَحَدُهُمَآ أَوۡ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَآ أُفّٖ وَلَا تَنۡهَرۡهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوۡلٗا كَرِيمٗا ٢٣ وَٱخۡفِضۡ لَهُمَا جَنَاحَ ٱلذُّلِّ مِنَ ٱلرَّحۡمَةِ وَقُل رَّبِّ ٱرۡحَمۡهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرٗا ٢٤ رَّبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَا فِي نُفُوسِكُمۡۚ إِن تَكُونُواْ صَٰلِحِينَ فَإِنَّهُۥ كَانَ لِلۡأَوَّٰبِينَ غَفُورٗا ٢٥)

‹‹ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፤- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፤በአንተ ዘንድ ኾነው፣አንዳቸው ወይም ሁለታቸው፣እርጅናን ቢደርሱ፣ፎህ አትበላቸው፤አትገላምጣቸውም፤ለነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው። ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፤ጌታዬ ሆይ! በሕጻንነቴ (በርኅራሄ) እንዳሳደጉኝ፣እዘንላቸውም በል። ጌታችሁ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው። ታዛዦችም ብትኾኑ፣(በመሳሳትም ብታጠፉ) እርሱ ለተመላሾች መሓሪ ነው።››

[አልኢስራእ፡23-25]

በተጨማሪም አላህﷻ እንዲህ ብሏል ፦

(وَوَصَّيۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيۡهِ حُسۡنٗاۖ وَإِن جَٰهَدَاكَ لِتُشۡرِكَ بِي مَا لَيۡسَ لَكَ بِهِۦ عِلۡمٞ فَلَا تُطِعۡهُمَآۚ إِلَيَّ مَرۡجِعُكُمۡ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ ٨ )

‹‹ሰውንም በወላጆቹ መልካም አድራጎትን አዘዝነው፤ላንተም በርሱ ዕውቀት የሌለህን (ጣዖት)፣በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው፤መመለሻችሁ ወደኔ ነው፤ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ።››

[አልዐንከቡት፡8]

2- የልጆች አያየዝ ፦

ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች መሆናቸውን አስመልክቶ አላህﷻ እንዲህ ብሏል ፦

( ٱلۡمَالُ وَٱلۡبَنُونَ زِينَةُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا)

‹‹ገንዘብና ወንዶች ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው፤››

[አልከህፍ፡46]

በሙእምኑ ልብ ውስጥ ያለው የአላህ ተውሒድ ልጆቹንና ቤተሰቡን በእስላማዊ መንገድ እንዲያሳድጋቸውና እንዲቀርጻቸው ያደርገዋል። አላህﷻ ምእመናን በኢማናቸው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከጀሀነም እሳት እንዲጠብቁ ጥሪ ሲያደርግላቸው እንዲህ ብሏል ፦

(يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ قُوٓاْ أَنفُسَكُمۡ وَأَهۡلِيكُمۡ نَارٗا وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلۡحِجَارَةُ عَلَيۡهَا مَلَٰٓئِكَةٌ غِلَاظٞ شِدَادٞ لَّا يَعۡصُونَ ٱللَّهَ مَآ أَمَرَهُمۡ وَيَفۡعَلُونَ مَا يُؤۡمَرُونَ ٦ )

‹‹እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጊያዎች ከኾነች እሳት ጠብቁ፤በርሷ ላይ ጨካኞች፣ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፤አላህን፣ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጡም፤የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ።››

[አልተሕሪም፡6]

ኃላፊነቱንም በያንዳንዱ ሰው ላይ አድርጓል። ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

#እያንዳንዳችሁ እረኞች ናችሁ፣ስለ መንጋዎቻችሁ ኃላፊነት አለባችሁ። ሕዝብ የሚያስተዳድር መሪ ለሕዝቡ እረኛ ነው፣ለመንጋው ኃላፊነት አለበት። ሰው በቤቱ ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ላይ እረኛ ነው፣ስለ መንጋው ኃላፊነት አለበት። ሚስት ለባልዋ ቤተሰብና ለልጆቹ እረኛ ነች፤ስለ መንጋው ኃላፊነት አለባት። የሰው አገልጋይ ለጌታው ንብረት እረኛ ነው፤ለዚሁም ኃላፊነት አለበት። ስለዚህ እያንዳንዳችሁ እረኞች ናችሁ፤ሁላችሁም በየራሳችሁ ኃላፊነት አለባችሁ።››

(በቡኻሪ የተዘገበ)

3 - ለሚስት የሚደረግ አያያዝ ፦

የተውሒድ ሰው ለሚስቱ ያለበትን ግዴታ ይወጣል፤በርሷ ነገር አላህን ያስባል። የሚገባትን ሲፈጽምና ደግነትን ሲያሳያት የአላህን ተቆጣጠሪነት እያሰላሰለ ነው። አላህﷻ እንዲህ ብሏል ፦

(وَلَهُنَّ مِثۡلُ ٱلَّذِي عَلَيۡهِنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِ)

‹‹ለነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም አኑዋኑዋር (በባሎቻቸው ላይ መብት) አላቸው፤››

[አልበቀራህ፡228]

ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹በላጫችሁ ለቤተሰቡ ከሌላው ይበልጥ ጥሩ የሆነ ሰው ነው፤እኔ ከሁላችሁም ይበልጥ ለቤተሰቤ ጥሩ ነኝ . . ››

(በትርምዚ የተዘገበ)

ሴቶች ባሎቻቸውን በመክሰስ ወደ አላህ መልክተኛ ﷺ ሲመጡ፣ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹ምርጦቻችሁ ለሴቶቻችሁ ምርጦች የሆናችሁ ናችሁ።››

(በእብን ማጃህ የተዘገበ)

4 - የባል አያያዝ ፦

ተውሒድ ወደ ጌታዋ ጀነት ትደርስ ዘንድ፣ለባሏ ያለባትን ግዴታ እንድትወጣ ምክንያት የሚሆን የአላህ ፍራቻ በሙእምኗ ሴት ልብ ውስጥ እንዲፈጠር ያደርጋል። ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹ሴት አምስት ወቅቷን ከሰገደች፣ወሯን (ረመዷንን) ከጾመች፣ብልቷን ከጠበቀችና ለባሏ ከታዘዘች፣ከጀነት በሮች በፈለግሽው ጀነት ግቢ፣ትባላለች።››

(በአሕመድ የተዘገበ)

አቅሙ የማይፈቅደውን ነገር እንዳትጠይቀውም አላህ አዟታል። አላህﷻ እንዲህ ብሏል ፦

(لِيُنفِقۡ ذُو سَعَةٖ مِّن سَعَتِهِۦۖ وَمَن قُدِرَ عَلَيۡهِ رِزۡقُهُۥ فَلۡيُنفِقۡ مِمَّآ ءَاتَىٰهُ ٱللَّهُۚ لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا مَآ ءَاتَىٰهَاۚ سَيَجۡعَلُ ٱللَّهُ بَعۡدَ عُسۡرٖ يُسۡرٗا ٧)

‹‹የችሎታ ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ፤በርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው፣አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድድም፤አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል።››

[አልጦላቅ፡7]

ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹ምንም ችግር ሳይኖር ባልዋን እንዲፈታት የጠየቀች ማንኛይቱም ሴት፣የጀነት ጠረን በርሷ ላይ ሐራም ሆኗል።››

(በአሕመድ የተዘገበ)

የዘመዶችና የጎረቤቶች አያያዝ ፦

አላህﷻ የርሱን ተውሒድና ዕባዳውን፣ሙእምኑ ሰው ለወላጆቹ፣ለዘመዶቹና ለጎረቤቶቹ ካለው አያያዝና ስነምግባር ጋር አቆራኝቷል። አላህﷻ እንዲህ ብሏል ፦

(وَٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَلَا تُشۡرِكُواْ بِهِۦ شَيۡٔٗاۖ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنٗا وَبِذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱلۡجَارِ ذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡجَارِ ٱلۡجُنُبِ وَٱلصَّاحِبِ بِٱلۡجَنۢبِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخۡتَالٗا فَخُورًا ٣٦ )

‹‹አላህንም ተገዙ፤በርሱም ምንንም አታጋሩ፣በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣በየቲሞችም፣በምስኪኖችም፣በቅርብ ጎረቤትም፣በሩቅ ጎረቤትም፣በጎን ባልደረባም፣በመንገደኛም፣እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው (ባሮች)፣መልካምን (ሥሩ)፤አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም።››

[አልኒሳእ፡36]

በተጨማሪም አላህﷻ እንዲህ ብሏል ፦

(فَئاتِ ذَا ٱلۡقُرۡبَىٰ حَقَّهُۥ وَٱلۡمِسۡكِينَ وَٱبۡنَ ٱلسَّبِيلِۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٞ لِّلَّذِينَ يُرِيدُونَ وَجۡهَ ٱللَّهِۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ ٣٨ )

‹‹የዝምድናን ባለቤት ተገቢውን ስጠው፤ለድኻም፣(እርዳ)፤ይህ ለነዚያ የአላህን ፊት (ውዴታውን) ለሚሹ መልካም ነው፤እነዚያም እነሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው።››

[አልሩም፡38]

ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው፣ለጎረቤቱ ደግ ይሁን . . ››

(በሙስሊም የተዘገበ)

ከሁሉም ሰዎች ጋር በሥራ ላይ ፦

ኢማን በተውሒድ ሰው ልብ ውስጥ መልካም ስነምግባርን ያንጻል። ለሰዎች ቅን፣በበይነሰባዊ ግንኙነቱም ላይ ሐቀኛ እንዲሆን ያደርገዋል። እነዚህ አንድ ሙእምን ወደ አላህﷻ የሚቃረብባቸው ምርጥ የትሩፋት ሥራዎች ናቸው።

1-

መልካም ስነምግባር ፦

አላህﷻ ስለ ነቢዩﷺ ባሕርይ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል ፦

(وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٖ ٤)

‹‹አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ።››

[አልቀለም፡4]

የአላህ መልክተኛﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹ሰዎችን በብዛት ወደ ጀነት የሚያስገባው የአላህ ፍራቻ (ተቅዋ) እና መልካም ስነምግባር ናቸው።››

(በትርምዚ የተዘገበ)

ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ ተወዳጁ ከሁሉም ይበልጥ ለሰዎች ጠቃሚ የሆነ ሰው ነው። አላህ ዘንድ ከሥራዎች ሁሉ ተወዳጁ ወደ አንድ ሙስሊም ልብ የምታስገባው ደስታ፣ወይም የምታስወግድለት ችግር፣ወይም የምትከፍለለት ዕዳ፣

ወይም የምታባርርለት ርሃብ ነው። ለጉዳዩ ብዬ ከአንድ ወንድሜ ጋር መሄድ በዚህ መስጊድ ውስጥ ለዕባዳ እዕትካፍ ከመቀመጥ ይበልጥ ለኔ የተወደደ ነው።››

(በጠበራኒ የተዘገበ)

2-

እውነተኛነት። አላህﷻ እንዲህ ብሏል ፦

(يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَكُونُواْ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ ١١٩)

‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ።››

[አልተውባህ፡119]

ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹እውነተኝነት ወደ በጎ ነገሮች ይመራል፤በጎ ነገሮች ደግሞ ወደ ጀነት ይመራሉ፤አንድ ሰው በጣም እውነተኛ እስከመሆን ድረስ እውነትን ይናገራል፤ውሸት ወደ ኃጢአት ይወስዳል፤ኃጢአት ደግሞ ወደ ጀሀነም እሳት ይወስዳል፤አንድ ሰው አላህ ዘንድ ውሸተኛው ተብሎ እስኪመዘገብ ድረስ ውሸትን ይናገራል።››

(በቡኻሪ የተዘገበ)

በተጨማሪም ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹የአስመሳይ (ሙናፍቅ) ሰው ምልክት ሦስት ነው ፦ ሲናገር ይዋሻል፤ቃል ሲገባ ያፈርሳል፤እምነት ሲጥሉበት ይክዳል።››

(በቡኻሪ የተዘገበ)

ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹አላህ መንጋ አስጠብቆት በሚሞትበት ቀን መንጋውን (በኃላፊነቱ ስር ያሉትን) ያታለለ ሆኖ የሚሞትን ማንኛውንም ሰው፣አላህ በርሱ ላይ ጀነትን ሐራም አድርጓል።››

(በሙስሊም የተዘገበ)

ነቢዩ ﷺ ሲተላለፉ የተከመረ እህል አዩና እጃቸውን ወደ ክምሩ ሰደዱ፤እጃቸውን ሲያወጡ ጣቶቻቸው ረጥበው ስለነበር ለባለቤቱ እንዲህ አሉት ፦

‹‹የእህል ባለቤት ይኸ ምንድን ነው?›› የአላህ መልክተኛ ሆይ! ዝናም ነክቶት ነው፣አላቸው። ‹‹ታዲያ የረጠበውን ሰዎች ያዩት ዘንድ ከደረቁ በላይ አታደርገውም ኖሯል? የሚያታልል ሰው ከእኔ ወገን አይደለም።››

(በሙስሊም የተዘገበ)

ነቢዩﷺ ኡመታቸውን የእስትንጃእ (የመጸዳዳት) ሥርዓት አስተምረው ተውሒድን ሳያስተምሩት ቀሩ ተብሎ ፈጽሞ ሊታሰብ አይችልም። ለዚህም ነው ነቢዩﷺ ፦ ‹‹ላ እላሀ እልላሏህ እስኪሉ ድረስ ሰዎችን እድዋጋቸው ታዝዣለሁ›› ያሉት። (በቡኻሪ የተዘገበ) የተውሒድ እውነታ ንብረትና ነፍስን የተጠበቀ የሚያደርግ ነው።

ኢማም ማሊክ ብን አነስ



Tags: