ሦስተኛ - አላህን ﷻ በስሞቹና በባሕርያቱ ዕወቀው

ሦስተኛ - አላህን ﷻ በስሞቹና በባሕርያቱ ዕወቀው
አላህﷻ እንዲህ ብሏል፦

(وَلِلَّهِ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ فَٱدۡعُوهُ بِهَاۖ وَذَرُواْ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ فِيٓ أَسۡمَٰٓئِهِۦۚ سَيُجۡزَوۡنَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ١٨٠)

‹‹ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፤(ስትጸልዩ) በርሷም ጥሩት፤እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፤ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ።››

[አልአዕራፍ፡180]

ሀ - የ (وَلِلَّهِ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ) ‹‹ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፤›› የሚለው ትርጉም ፦

የአላህﷻ ስሞች ሁሉም የሚያሞግሱ ስሞች ናቸው። አላህﷻ ሁሉን ስሞቹን መልካም መሆናቸውን ገልጾአል። አላህﷻ እንዲህ ብሏል፦

(وَلِلَّهِ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ فَٱدۡعُوهُ بِهَاۖ وَذَرُواْ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ فِيٓ أَسۡمَٰٓئِهِۦۚ سَيُجۡزَوۡنَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ١٨٠)

‹‹ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፤(ስትጸልዩ) በርሷም ጥሩት፤እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፤ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ።››

[አልአዕራፍ፡180]

መልካሞች የሆኑት ለቃላቸው ንበት ብቻ ሳይሆን የምሉእነት ባሕርያትን የሚያመለክቱ በመሆናቸው ነው። ሁሉም ስሞች እርሱን የሚያሞግሱት፣የሚያወድሱትና የሚያልቁት ስሞች ናቸው። ለዚህም ነው መልካሞች የሆኑት። ባሕርያቱም እንደዚሁ ሁሉም የምሉእነት ባሕርያት ናቸው። መገለጫዎቹ ሁሉ የልዕልና፣የልቅና እና የግርማ ሞገስ መገለጫዎች ናቸው። ሁሉም ሥራዎቹ የጥበብ፣የእዝነት፣የጥቅምና የፍትሕ ሥራዎች ናቸው።

በአላህ ስሞችና በባሕርያቱ በርሱ መጽሐፍና በነቢዩﷺ ሱንና ውስጥ በተመለከተው መሰረት ማመን፣የኢማን አንድ አካል ነው። በአስማእና በስፋት ማመን በሁለት መሰረታዊ መርሕ ላይ የታነጸ ነው።

የመጀመሪያው መርሕ ፦

የአላህን ስሞች ሳያጣምሙ፣ትርጉም የለሽ ሳያደርጉ፣ከሌላው ጋር ሳያመሳስሉና አኳኋኑ እንዲህ ነው ሳይሉ ለርሱ ግርማ ሞገስና ለኃያልነቱ ተገቢ በሆነ መንገድ ማረጋገጥ ነው። አላህﷻ እንዲህ ብሏል፦

(لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ١١)

‹‹የሚመስለው ምንም ነገር የለም፤እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው።››

[አልሹራ፡11]

ሁለተኛው መርሕ ፦

ትርጉሞቹን መረዳት፣ስሞቹ የያዟቸውን ባሕርያት (ስፋት) ትክክለኛ አኳኋናቸውን ሙሉ በሙሉ ለመገንዘብ ካለመሞከር ጋር ማረጋገጥ ነው። አላህﷻ እንዲህ ብሏል፦

(يَعۡلَمُ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡ وَلَا يُحِيطُونَ بِهِۦ عِلۡمٗا١١٠)

‹‹በስተፊታቸው ያለውን፣በስተኋላቸውም ያለውን ሁሉ ያውቃል፤በርሱም ዕውቀትን አያካብቡም፤(አያውቁም)።››

[ጣሃ፡110]

አላህﷻ በመልካም ስሞቹና በላቁ ባሕርያቱ ለባሮቹ ራሱን ለምን ዓለማ እንዳስተዋወቀ የገለጸ ሲሆን፣እሱም በስሞቹና በባህርያቱ እንዲግገዙት ነወ። አላህﷻ እንዲህ ብሏል፦

(قُلِ ٱدۡعُواْ ٱللَّهَ أَوِ ٱدۡعُواْ ٱلرَّحۡمَٰنَۖ أَيّٗا مَّا تَدۡعُواْ فَلَهُ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ)

‹‹፦ አላህን ጥሩ፤ወይም አልረሕማንን ጥሩ፤(ከሁለቱ) ማንኛውንም ብትጠሩ፣(መልካም ነው)፤ለርሱ መልካም ስሞች አሉትና በላቸው፤››

[አልኢስራእ፡110]

በተጨማሪም አላህﷻ እንዲህ ብሏል፦

(وَلِلَّهِ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ فَٱدۡعُوهُ بِهَاۖ وَذَرُواْ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ فِيٓ أَسۡمَٰٓئِهِۦۚ سَيُجۡزَوۡنَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ١٨٠)

‹‹ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፤(ስትጸልዩ) በርሷም ጥሩት፤እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፤ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ።››

[አልአዕራፍ፡180]

ለ - (فَٱدۡعُوهُ بِهَا) ‹‹በርሷም ጥሩት፤›› ማለት ፦

በመልካሞቹ ስሞቹ እርሱን መጥራት ማለት ሁለት ዓይነት መጥራትን (ዱዓእን) የሚያካትት ሲሆን፣‹‹አላህ ሆይ! ስጠኝ፣በጣም አዛኙ ሆይ! እዘንልኝ! በጣም ቸር የሆንከው ጌታ ከችሮታህ ስጠኝ›› ማለትን የመሳሰለው የልመና ጥሪ አንዱ ነው። ሌላው የውዳሴና የአምልኮ ጥሪ (ዱዓእ) ሲሆን፣ልመና ሳይኖርበት አላህንﷻ በስሞቹና በባህርያቱ ማወደስና ማላቅን የመሳሰለ ነው። ውዳሴው በልብ ወይም በምላስ የመልካም ስሞችና የላቁ ባሕርያት ባለቤት የሆነውን አላህንﷻ በማስታወስና በመዘከር ሊሆን ይችላል።

ሐ - (وَذَرُواْ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ) ‹‹እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፤›› ማለት ፦

የአላህን ስሞች ማጣመም ማለት በአላህﷻ መጽሐፍ ውስጥ የቀረበውን ነገር ማስተባበል፣ወይም ስሞቹን ከፍጥረታቱ ስሞች ጋር ማመሳሰል፣ወይም አላህን ﷻ ለርሱ ተገቢ ባልሆነ በቁርኣንም ሆነ በነቢዩﷺ ሱና ውስጥ ማስረጃ በሌለው ስም መሰየም ወይም ባሕርይ (ስፋህ) እርሱን መግለጽ ማለት ነው።Tags: