በስሞቹና በባሕርያቱ ማመን በባሪያው ላይ የሚያሳርፈው አሻራ፦

በስሞቹና በባሕርያቱ ማመን በባሪያው ላይ የሚያሳርፈው አሻራ፦
1- በአላህﷻ ስሞችና በባሕርያቱ እርሱን ማምለክ፦ አንድ አገልጋይ ስሞቹንና ባሕርያቱን ካወቀ ጌታው በሚፈልገው መንገድ ያምንባቸዋል። በጌታው ያለውን እምነት በሚያሳድግ ሁኔታ ትርጉማቸውን ይረዳል።እርሱን ባወቀ ሰው ልብ ውስጥ የአላህﷻ ኃያልነትና ግርማ ሞገሱ ስር ይሰዳል። ለዚህ ነው ‹‹አላህን ይበልጥ የሚያውቅ ከማንም ይበልጥ እርሱን ይፈራል›› የተባለው።

2 - የኢማን መጨመር ፦

የአላህንﷻ መልካም ስሞችና የላቁ ባሕርያቱን ማወቅ፣የአላህንﷻ ኃያልነትና ግርማ ሞገሱን የመገንዘብ ስሜት በአገልጋዩ ልብ ውስጥ እንዲፈጠር ያደርጋል። ይህም በኢማኑ ላይ ኢማንን፣ለአላህﷻ ባለው መተናነስና ተገዥነት ላይ የበለጠ መተናነስንና ተገዥነትን ይጨምርለታል።

(وَٱلَّذِينَ ٱهۡتَدَوۡاْ زَادَهُمۡ هُدٗى)

‹‹እነዚያም የተመሩት፣(አላህ) መመራትን ጨመረላቸው፤››

[ሙሐመድ፡17]

2-

የአላህ ﷻ ውዳሴ ፦

አላህን ያወቀ ሰው ይወደዋል፤ጌታውን የወደደ ሰው ደግሞ፣ልቡ ሙሉ በሙሉ ለፍቅሩ የተገዛ በመሆኑ የርሱን ውዳሴ ያበዛል። ውዴታው ሌሎችን ለርሱ ብቻ ብሎ እስከመውደድና ለርሱ ብቻ ብሎ እስከመጥላት ደረጃ ይዘልቃል።

አላህﷻ እንዲህ ብሏል፦

(وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَندَادٗا يُحِبُّونَهُمۡ كَحُبِّ ٱللَّهِۖ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَشَدُّ حُبّٗا لِّلَّهِ)

‹ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባላንጣዎችን (ጣዖታትን)፣አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፤እነዚያ ያመኑትም፣አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፤››

[አልበቀራህ፡165]

አንድ አገልጋይ የአላህንﷻ ባሕሪ ኃያልነት ሲያውቅ ነፍሱ ወደ ጌታው ታዘነብላለች፤በርሱምﷻ ትንጠለጠላለች። በግርማ ሞገሱና በውበቱ ምሉእነት ነፍሱ ትፈነድቃለች። በዚህም አገልጋዩ በአልረሕማን ንግግር (በቁርኣን) ጥፍጥና ይደሰታል፤እርሱን በመጥራት፣ተስፋውን በርሱ ላይ በመጣልና እርሱን ብቻ በመፍራት ይጽናናል። የአላህﷻ ውዴታ ወደዚያ የሚገፋፋው በመሆኑ አላህን ሲወድ፣አላህ የሚወደውን ነገርና አላህ የሚወደውን ሰው ሲወድ እናገኛዋለን።

5 - አላህንﷻ ማፈር ፦

አንድ አገልጋይ አላህንﷻ ባወቀ ቁጥር የበለጠ ያከብረዋል፣ያልቀዋል። የበለጠ ባከበረውና ባላቀው መጠንም እርሱን ማፈሩ ይጨምራል፤ሞትን አስታውሶ ያለቅሳል፤አካላቱን አላህﷻ ከማይወደው ነገር ይጠብቃል።

6 - ራስን ለርሱ ማስተናነስና ለርሱ ማደግደግ፦

የአላህንﷻ ኃያልነት ካወቅህ የራስህን ኢምንትነት ታውቃለህ። የርሱን አቅምና ችሎታ ካወቅህ ያራስህን ደከማነት አውቀህ ትቀበላለህ። የርሱን ፍጹማዊ መብቃቃት ካወቅህ የራስህን ድህነት ታውቃለህ። የርሱን ፍጹማዊ ምሉእነት ካወቅህ የራስህን እንከንና ጉድለት ታውቃለህ። የባሕርያቱን ምሉእነትና የስሞቹን ውበት ካወቅህ፣አንተ ተገዥ ባሪውያው እንጅ ሌላ አይደለህምና የራስህን ጉድለት፣ድህነት፣ደካማነትና አቅም የለሽነት ትገነዘባለህ።

ማንም ሰው የአላህንﷻ እርሱነትና ባሕርያቱን በተመለከተ እርሱ ራሱን ከገለጸበት ውጭ በምንም ነገር እርሱን መግለጽ የለበትም። እርሱን አስመልክቶ በገዛ ሀሳቡ ምንም ነገር ማለት የለበትም፤እርሱ የልቅና ባለቤት የሆነ የጠራ የዓለማት ጌታ ነውና።

ኢማም አቡ ሐኒፋ



Tags: