በአላህ የማመን ጽንሰ ሀሳብና ትክክለኛ ምንነቱ፦

በአላህ የማመን ጽንሰ ሀሳብና ትክክለኛ ምንነቱ፦
እውነተኛ ሃይማኖት የመንፈስ ሕይወትና የሚደሰቱበት የመዝናኛ ሜዳ ነው

በአላህ ማመን

በአላህ የማመን ጽንሰ ሀሳብና ትክክለኛ ምንነቱ፦

እውነተኛ ሃይማኖት የመንፈስ ሕይወትና የሚደሰቱበት የመዝናኛ ሜዳ ነው

የመንፈስ ደስታና የነፍስ እርካታ በአላህ ﷻ በማመን ብቻ እንጂ ሊገኝ አይችልም። ያላመነች ነፍስ የፈራች፣የባዘነች፣ደካማና ያልተረጋጋች ሆና ትቀራለች። ለመድህን የሚያበቃው ኢማን በአላህ ማመን ሲሆን፣ትርጉሙ አላህ ﷻ የሁሉም ነገር ጌታ፣ንጉሥና ፈጣሪ መሆኑን በቁርጠኝነት አምኖ ማረጋገጥ ነው። ሶላትን፣ጾምን፣ጸሎትን፣ተስፋ ማድረግን፣ፍርሃትን፣ መተናነስን፣ተገዥነትን . . የመሳሰለ የዕባዳ ዓይነት ለርሱ ﷻ ብቻ የሚገባ መሆኑን፣በሁሉም የምሉእነት በህርያት የሚገለጽ፣ከእንከንና ከጉድለቶች ሁሉ ፍጹም የጠራ መሆኑን ማመን ማለት ነው።

በአላህ ﷻ ማመን በመላእኮቹ፣በመልክተኞቹ፣በመጻሕፍቱ፣በመጨረሻው ቀን፣በጎውም ሆነ መጥፎው በርሱ ዕውቅናና በቅድመ ውሳኔው የሚከሰት መሆኑን ማመንን ያካትታል። ይህ እምነትም ለሰው ልጅ የደስተኝነትና የመታደል መሰረት ብቻ ሳይሆን፣ለአማኙ ሰው ፍጻሜው በአላህ ፈቃድ የኣኽራ ጀነት የሚሆን የዛሬ የዱንያ ሕይወት ጀነትም ነው።

‹‹ኢማን (እምነት) ሸሪዓዊ ትርጉሙ በልብ አምኖ በመቀበል በአንደበትም ማረጋገጥ ነው።››

ይህ ከታወቀ፣ሥራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ዋናው መሰረታዊ መስፈርት ኢማን ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏልና፦

(فَمَن يَعۡمَلۡ مِنَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ)

‹‹እርሱ ያመነ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች ማንኛውንም የሚሠራም ሰው፤።››

[አልአንቢያ፡94]

በአላህ ማመን ወደ ፍትሕ የሚመራ ብርሃን ነው። ወደ ነጻነት የሚመራ ብርሃን ነው። ወደ እውቀትና ትምሕርት የሚመራ ብርሃን ነው። ወደ ቅን መንገድ የሚመራ ብርሃን ነው። ወደ ሕሊና እርካታና ወደ መንፈስ መረጋጋት የሚመራ ብርሃን ነው።

የኢማን አስፈላጊነት

አላህ ዘንድ ከሥራዎች ሁሉ በላጩና ተወዳሹ ኢማን ነው። ይህም አቡ ዘር (ረዐ) እንዲህ በማለት ለአላህ መልክተኛ ﷺ ባቀረቡትና በተሰጣቸው መልስ መሰረት ነው፦

‹‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከሥራዎች ሁሉ በላጩ የትኛው ነው?›› ብለው ሲጠይቁ፣ነቢዩ ﷺ ፦ ‹‹በአላህ ማመንና በርሱ መንገድ መታገል ነው›› አሉ።

(በሙስሊም የተዘገበ)

ወደ ቅኑ መንገድ ለመመራት፣የዱንያና ኣኽራን ተድላና ደስታ ለመጎናጸፍም መነሻ ምክንያት ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(فَمَن يُرِدِ ٱللَّهُ أَن يَهۡدِيَهُۥ يَشۡرَحۡ صَدۡرَهُۥ لِلۡإِسۡلَٰمِ

‹‹አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለእስላም ይከፍትለታል፤››

[አልአንዓም፡125]

ኢማን አማኙን ከአላህ ትእዛዝ ጥሰት እንዲታቀብ ያደርገዋል። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ إِذَا مَسَّهُمۡ طَٰٓئِفٞ مِّنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ تَذَكَّرُواْ فَإِذَا هُم مُّبۡصِرُونَ ٢٠١)

‹‹እነዚያ የተጠነቀቁት፣ከሰይጣን የኾነ ዟሪ በነካቸው ጊዜ፣(ጌታቸውን) ይገነዘባሉ፤ወዲያውም እነሱ ተመልካቾች ይኾናሉ።››

[አልአዕራፍ፡201]

ኢማን ሥራዎች አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ መሟላት ያለበት መስፈርት (ሸርጥ) ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

(وَلَقَدْ أُوحِيَ إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ)

‹‹ብታጋራ፣ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፤በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል።››

[አልዙመር፡65]

በጠራና ፍጹም በሆነ ኢማን አላህ ﷻ ሥራን ብሩክ ያደርጋል፣ጸሎትና ልመናንም እርሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደርጋል።

(وَلَقَدْ أُوحِيَ إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ)

‹‹ብታጋራ፣ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፤በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል።››

[አልዙመር፡65]

በጠራና ፍጹም በሆነ ኢማን አላህ ﷻ ሥራን ብሩክ ያደርጋል፣ጸሎትና ልመናንም እርሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደርጋል።Tags: